Interview

የስኳር በሽታ ... ከዶ/ር አህመድ ረጃ የውስጥ ደዌ ሰፔሻሊስት ጋር ጥቂት ቆይታ

ዶ/ር በመጀመሪያ የተጣበበ ጊዜዎትን አብቃቅተው እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ፍቃደኛ በመሆንዎ ከልብ የሆነ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን።

 1. ፋርማኔት፡- አሁን የሚሰሩበትን ቦታ እና ምን ምን አይነት ሀላፊነት እንዳሎት ለአንባቢያን ቢገልፁልን?

ዶ/ር አህመድ፡- የሥራ ቦታ፡- በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በውስጥ ደዌ የትምህርትና ሕክምና ክፍል

ኃላፊነት፡- የውስጥ ደዌ የትምህርት ሕክምና ክፍል ኃላፊ

- የስኳር ህመም ህክምና ክፍል ኃላፊ

- የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ኘሬዚዳንት

- የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ብሔራዊ ማህበር የቦርድ ም/ኘሬዚዳንት

 1. ፋርማኔት፡- እንደሚታወቀው የስኳር በሽታ ለአብዛኛዎቹ የህብረተሰባችን ክፍል ስጋት ነው፤ ስለዚህ በሽታ ምንነት እና ስለስኳር በሽታ አይነቶች ጥቂት ቢገልጡልን?

ዶ/ር አህመድ፡- ስለስኳር ህመም ምንነት ለመረዳት ሶስት ነገሮችን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ሀ/ ስለቆሽት

ለ/ ስለ ኢንሱሊን

ሐ/ ስለሥርዓተ ልመት (Digestion System)

አንድ ሰው ምግብ በሚበላበት ጊዜ በጨጓራና አንጀት በሚካሄዱ ተከታታይ ኬሚካላዊ ለውጦች ምግቡ ወደ ስኳር ይለውጣል፡፡ ይህ ስኳር በደም ዝውውር አማካይነት ወደ ተለያዩ የሰውነት ህዋሳት በመግባት በኃይል ምንጭነት ያገለግላል፡፡ ይህ ስኳር ወደ ህዋሳት እንዲሰርግ ታዲያ ኢንሱሊን የተባለ ንጥረ ቅመም ያስፈልጋል፡፡ ኢንሱሊን የሚገኘው ደግሞ ቆሽት ከተባለ የሰውነት ክፍል ነው፡፡

ቆሽት የተባለው የሰውነት ክፍል ኢንሱሊንን የማምረት ተግባሩ ሲስተጓጐል ስኳሩ ወደ ህዋሳት መስረግ ስለሚያቅተው በደም ውስጥ ይጠራቀማል፡፡ የስኳር ህመም መገለጫው ደግሞ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ሲል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሰው የስኳር ህመም አለበት የሚባለው በባዶ ሆድ በሚደረገው ምርመራ በደሙ ውስጥ ያለው ስኳር ከ126 ሚ.ግ በዲሲ ሊትር በላይ ሲሆን ነው፡፡

የስኳር ህመም ዓይነቶች

 1. አንደኛው ዓይነት የስኳር ህመም (Type 1 Diabetes)
 2. ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም (Type 2 Diabetes)
 3. ከሌሎች ህመሞችና መድሃኒቶች ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስኳር ህመም (Specific forms of Diabetes)
 4. እርግዝና ነክ የስኳር ህመም (Gestational Diabetes)

አንደኛው ዓይነት የስኳር ህመም ዕድሜአቸው እስከ 30 ዓመት የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍል ይይዛል፣ የስኳር ህመም ምልክቶች በጉልህና አጣዳፊ ሁኔታ ይታያሉ፡፡ ቆሽት ኢንሱሊን የማምረት ተግባሩ ሙሉ ለሙሉ ስለሚቆም ይህ ዓይነት የስኳር ህመም የያዛቸው ህፃናትና ወጣቶች ያለማቋረጥ ዕድሜ ልክ የኢንሱሊን መርፌ በመወጋት ስኳራቸው መቆጣጠር ይኖርባቸዋል፡፡

ሁለተኛ ዓይነት የስኳር ህመም

- ዕድሜአቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎችን ይይዛል፡፡

- የስኳር ህመም ምልክቶች ጉልህና አጣዳፊ ሆነው ብዙ ጊዜ አይታዩም፡፡ እንዲያውም ይህ ዓይነት የስኳር ህመም በአጋጣሚ ለሌላ ጉዳይ ምርመራ ሲደረግ /ማለት ለሥራ፣ ለኢንሹራንስ፣ ለመንጃ ፈቃድ ወይም ለሌላ የጤና ችግር/ የሚታወቀበት ሁኔታ በብዛት ይታያል፡፡

- ቆሽት ኢንሱሊን የማምረት ተግባሩ ይቀንሳል፡፡

- ይህ ዓይነት የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች በእንክብል የሚታከሙ ሲሆን ከዓመታት በኋላ ቆሽት ኢንሱሊን ማምረት ሲያቅተው የኢንሱሊን መርፌ ይታዘዝላቸዋል፡፡

 1. ፋርማኔት፡- ዶ/ር ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች የሚታይባቸው ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር አህመድ፡- የስኳር ህመም ምልክቶች

- የማይረካ ከፍተኛ የውሃ ጥማት

- በብዛትና ቶሎ ቶሎ መሽናት

- ከፍተኛ የረሃብ ስሜትና ከበሉም በኋላ ወዲያው መራብ

- ክብደት መቀነስ

- አቅም ማጣት

 

ዶ/ር አህመድ፡-

የስኳር ህመም በባህላዊ መንገድም ሆነ በሳይንሳዊ ዘዴ ማዳን አይቻልም:: ነገር ህመሙን ተቆጣጥሮ ጤናማ ኑሮ መኖር ይቻላል፡፡

ስኳር ህመም በፍጥነት እየጨመረ ያለ አሳሳቢ የማህበረሰባችን የጤና ችግር ነው፡ ፡ በመሆኑም ሁሉም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ተኩረት ሰጥተውት በመከላከል ተግባር ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

የእይታ ብዥ ማለት

- ሴቶች ማህፀን አካባቢ ማሳከክ

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ግን እነዚህ ምልክቶች ሁሉም ህሙማን ላይ በአንዴ ይታያሉ ማለት አይደለም፡፡ ምልክቶቹ ሁሉም ላይ ሊታዩ ቢችሉም በጉልህና በአጣዳፊ የሚታዩት ግን አንደኛ ዓይነት የስኳር ህመም ባለባቸው ሰዎች ላይ ነው፡፡

የስኳር ህመም ምልክቶች ሳያሳይ ለብዙ ዓመታት ቆሽቱ ውስጥ ውስጡን ሊጐዳ የሚችል ህመም መሆኑን ልብ ሊሉት የሚገባ ጉዳት ነው፡፡

 1. ፋርማኔት፡- የስኳር በሽታ በምን ምን ምክንያቶች እንደሚከሰት እንደሚይዝ ቢነግሩን፡፡

ዶ/ር አህመድ፡- የስኳር ህመም ትክክለኛ መንስኤ እስከአሁን ድረስ አይታወቅም የሚታወቀው ነገር የስኳር ህመም የሚከሰተው ቆሽት ኢንቡሊንን የማምረት ተግባር ሲስተጓጐል መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን የቆሽት ተግባር ለምንድነው የሚስተጓጐለው የሚለው ነገር እስከአሁን ድረስ ሊደረግበት ያልተቻለ ፈታኝ እንቆቅልሽ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ለስኳር ህመም በተለይም ለሁለተኛው ዓይነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች አሉ፡፡

እነሱም፡-

 1. ዕድሜው ከ45 ዓመት በላይ የሆነ
 2. በቅርብ የቤተሰብ አባል የስኳር ህመም መኖር
 3. ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ሥርዓት መከተል
 4. የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ
 5. የሰውነት ትርፍ ክብደትና ውፋሌ
 6. ሲጋራ ማጨስ
 7. የደም ግፊት መጨመር
 8. በደም ውስጥ የቅባት መጠን መጨመር
 9. ከ4 ኪሎ ግራም በላይ የሆኑ ህፃናትን የወለዱ ሴቶች
 10. በእርግዝና ወቅት የስኳር ህመም ታይቶባቸው ከወሊድ በኋላ የጠፈላቸው ሴቶች በቀጣዩ እርግዝናም ሆነ በቀጣዩ ህይወታቸው ለስኳር ህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡
 11. ፋርማኔት፡- አንድ ሰው የስኳር በሽታ እንዳይዘው ለመከላከል ምን ማድረግ አለበት?

ዶ/ር አህመድ፡-

- ጤናማ አመጋገብ መከተል

- ተከታታይነት ባለው መልኩ አዘውትሮ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ

- ትርፍ ክብደት /ከቁመት ጋር የማይመጣጠን/ ማስወገድ

- ሲጋራ አለማጨስ

 

 1. ፋርማኔት፡-የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሳይንስ ምን አይነት ምግቦችን እንዲመገቡ ይመከራል?

ዶ/ር አህመድ፡-

- ስኳርነት ያለባቸው ምግቦች ማስወገድ

- ቅባት እጅጉን መቀነስ

- አለርነት ያለባቸው ምግባች በብዛት መመገብ

- ከጥጋብ በላይ አለመመገብ

- ምግብ ሲበሉ ቶሎ ቶሎ አለመብላት

- የምግብ ሰዓት ጠብቆ መብላት

 

 1. ፋርማኔት፡- የኤች ቢ ኤዋን ሲ ምርመራ ምንነት ጥቂት ቢያጫውቱን?

ዶ/ር አህመድ፡- በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከቀን ወደ ቀን ይለዋወጣል፣ ዛሬ ደህና የነበረው ነገ ከፍ ወይ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡

ይህ ምርመራ የሚነግረን ላለፉት 3 ወራት የስኳር ቁጥጥሩ ምን ደረጃ ላይ እንደነበር ነው፡፡

 

 1. ዶ/ር ከስኳር በሽታ የተነሳ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ተያያዥ የጤና ችግሮች ጥቂት ቢነግሩን?

ዶ/ር አህመድ፡- ለዓመታት በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም የሚከተሉትን የረጅም ጊዜ ጠንቆች ሊያስከትል ይችላል፡፡

- የዓይን ጉዳት እስከ ብርሃን ማሳጣት

- የኩላሊት ጉዳትና መድከም

- የነርቭ ጉዳት

- የልብ ጉዳት

- የአንጐል የደም ዝውውር መታወክ/ስትሮክ/

 

- የእግር የደም ዝውውር መታወክ / ጋንግሬን/

- የእግር መቁሰል

- የጥርስና የድድ ችግር

- የቆዳ ማሳከክ

- የመገጣጠሚያዎች ችግር

 1. ፋርማኔት፡- በስኳር በሽተኞች ላይ ስለሚፈጠረው የዕይታ ችግር ጥቂት ቢያብራሩልን?

ዶ/ር አህመድ፡- የስኳር ህመም በአግባቡ ካልተቆጣጠሩት የዕይታ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ ችግሮቹም

- የዓይን ሞራ

- የዓይን ጀርባ /ሬቲና/ ያሉ የደም ቧንቧዎች

በመዝጋት ወይም ደሞ በመፍሰስ፣ ዕይታ ሊቀንስና ሊጠፋ ይችላል፡፡ ይህ ለመከላከል ሲያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዓይን ሐኪም ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

image
image
 1. ፋርማኔት፡- የስኳር በሽታ ታክሞ መዳን ይችላል? ከተቻለ አሁን በሀገራችን ላይ እንዴት እየታከመ ይገኛል?

ዶ/ር አህመድ፡- የስኳር ህመም በባህላዊ መንገድም ሆነ በሳይንሳዊ ዘዴ ማዳን አይቻልም ነገር ህመሙን ተቆጣጥሮ ጤናማ ኑሮ መኖር ይቻላል፡፡

 1. ፋርማኔት፡- የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ጤንነቱን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?

ዶ/ር አህመድ፡-

- ህመሙን በፀጋ መቀበል

- ስለስኳር ህመም ግንዛቤውን ለማስፋት ትምህርት መውሰድና ትምህርቱን በተግባር መተርጐም

- ጤናማ አመጋገብ መከተል

- አዘውትሮ ቢያንስ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

- መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ

- ሲጋራ አለማጨስ

- ወቅታዊ የአካለና የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ

 1. ፋርማኔት፡- የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር እርሶ አንድ አካል ኖት፣ እስቲ ማህበሩ ምን እየሰራ እንዳለ እና ለወደፊት ምን እንዳቀደ ጥቂት ቢያወጉን?

ዶ/ር አህመድ፡-

- ለህሙማን እና ቤተሰቦቻቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የወሩን የመጨረሻ ቅዳሜ ይዞ ከሰባት ሰዓት በኋላ በተለያዩ ርርሶች ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን በመጠቀም ትምህርት ይሰጣል፡፡

- በራሪ ጽሑፎችንና መጽኤት /ልሳነ ስኳር ህመም/ ያዘጋጃል፡፡

- በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በመገኘት ለሠራተኞች በስኳር ህመም ዙሪያ ትምህርት መስጠት

- የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለህሙማን እና ለሕብረተሰቡ ማስተማር

- ለህፃናት ስኳር ህሙማን በነፃ ኢንቡሊን፣ የደም መመርመሪያ መሳሪያ መስጠት

- ለስኳር ህሙማን በነፃ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የዓይን ምርመራና ህክምና መስጠት

- በተለያዩ ክልሎች ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች በማቋቋም ትምህርትና ግልጋሎት መስጠት በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች 35 ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች አሉን፡፡

- በየዓመቱ የዓለም የስኳር ህመም ቀንን በእግር ጉዞ፣ በትምህርታዊ ሴሚናና ወዘተ ማክበር

- ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በቅርብ በመሥራት በስኳር ህመም ዙሪያ ማማከር

 1. ፋርማኔት፡- ዶ/ር የስኳር በሽታን ለመመርመር በግል የምንጠቀምባቸው የተለያዩ አነስተኛ መሳሪያዎች ምንነት እና አጠቃቀም ጥቂት ቢያወጉን?

ዶ/ር አህመድ፡- እነዚህ መሳሪያዎች ቢቻል እያንዳንዱ ህመምተኛ ሊኖረው የሚገባ ነው፡፡ ውድ ከመሆናቸው የተነሳ ግን ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የሚጠቀሙባቸው፤ ከጣት ላይ ጥቂት ደም በመውሰድ እቤት ውስጥ ራስን ለመመርመር የሚረዱ ጠቃሚ መሳሪዎች ናቸው፡፡ አጠቃቀማቸው ቀላል ነው፡፡

 1. ፋርማኔት፡- ዶ/ር በመድሐኒት አወሳሰድ ዙሪያ የስኳር በሽታ ላለባችው ሰዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ይኖራልን?

ዶ/ር አህመድ፡- ሐኪሞች በሚያዙት መሰርት መድሐኒት መውሰድ

ተሸሎኛል ብሎ መድሐኒት አለማቋረጥ

መድሐኒት የሚወሰድበትን ሰዓት ጠብቆ መውሰድ

 1. ፋርማኔት፡- ዶ/ር በግልዎ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ?

ዶ/ር አህመድ፡- ስኳር ህመም በፍጥነት እየጨመረ ያለ አሳሳቢ የማህበረሰባችን የጤና ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ተኩረት ሰጥተውት በመከላከል ተግባር ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

I believe that a simple and unassuming manner of life is best for everyone, best both for the body and the mind.

Albert Einstein

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and typesetting industry. Lorem Ipsum has been the industry's standard dummy text ever since the 1500s, when an unknown printer took a galley of type and scrambled it to make a type specimen book. It has survived not only five centuries, but also the leap into electronic typesetting, remaining essentially unchanged. It was popularised in the 1960s with the release of Letraset sheets containing Lorem Ipsum passages, and more recently with desktop publishing software like Aldus PageMaker including versions of Lorem.

Social & newsletter

Search