Business

አስገራሚ የምጥ ታሪኮች

  1. ማራቶንን ከሮጠች በኋላ የወለደችው እናት

 

አንበር ሚለር ትባላለች የ9 ወር እርጉዝ ሆና ሣለች ነበር በአለም ላይ ታዋቂ የሆነውን የቺካጐ ማራቶን ከባሌ ጋር እሮጣለሁ ብላ ወደ ውድድሩ በድፍረት የገባችው፡፡ ልትወልድ የቀራት ቀን በጣት የሚቆጠር ሆኖ ሣለ ይህን ውሣኔ ማድረግ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ በሩጫው መሐል ምጥ የመጣባት ሚለር ምጧን ታግሣ ውድድሩን ለመጨረስ 6 ሰዓታት፣ 25 ደቂቃዎች ከ50 ሰከንዶች ወስዶባታል፡፡ ሚለር ሩጫዋን ከጨረሰች በኋላ ሴት ልጇን በሰላም ተገላግላለች፡፡

 

  1. ኪክ ቦክሲንግ ውድድር ላይ የወለደችው ታዳጊ

 

ኪክ ቦክሲንግ ውድድር ላይ የወለደችው ታዳጊ /እርጉዝ መሆኗን አታውቅም ነበር/ የ17 አመቷ የሪንግ ተደባዳቢ ፓሜላ ከተጋጣሚዋ ጋር በመደባደብ ላይ ሣለች ሆዷን በመመታቷ ደም ይፈሣታል፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰዎች በአንቡላንስ ይዘው በአቅራቢያ ሆስፒታል ያደርሷታል፡፡ በዚህ ወቅት ብዙዎች ያስገረመ ነገር ከህክምና ባለሙያዎቹ ተሰማ ፖሜላ ለግጥሚያ ስትገባ የ7 ወር እርጉዝ ነበረች፡፡ በተደረገላት እርዳታም ሴት ልጅ በሠላም ተገላግላለች፡፡

 

  1. በህክምና አጠራር ሞተች (Brain Dead) የተባለች ሴት መንታ ወለደች ፡-

 

በህክምና አንድ ሰው አዕምሮው መስራት አቆመ ማለት ሞተ ማለት ነው በሚችጋን ነዋሪ የሆነችው ክሪስቲን ቦልደን ድንገት መንገድ ላይ ትወድቃለች፡፡ ወደ ህክምና ተቋም ከደረሰች በኋላ ሀኪሞች እንደሞተች ያረጋግጣሉ በሆዷ ውስጥ ያሉትን ልጆች ለማዳን በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ከወር በኋላ መንታ ልጆች ተገኝተዋል፡፡ ክሪስቲን ቦልዳን በተደረገላት የህይወት ማቆያ ድጋፍ ልጀቿ በህይወት ሲተርፉ እርሷ ግን እስከ ወዲያኛው አሸልባለች፡፡

image
image
  1. የሜክሲኮዋ ተወላጅ ራሚሬዝ በሊፍት ውስጥ ወልዳለች፡፡

 

በአጋጠማት የምጥ ህመም ወደ ህክምና ተቋም የሄደችው ራሚሬዝ በነርሷ በተደረገላት ምርመራ ለመውለድ አለመድረሷ ተነግሯት ወደ ቤቷ ትመለሣለች፡፡ ባሏ በመኪና አድርሷት ወደ ስራው ሲመለስ አፖርታማ ፎቅ የሚገኘው ቤቷ እስክትደርስ ድረስ ምጧ ጊዜ አልሠጣትም፡፡ የአፓርታማው ሊፍት ውስጥ ወንድ ልጅ ልትገላገል ችላለች፡፡

 

  1. እስር ቤት ወለል ላይ የወለደችው እናት

 

የ29 አመቷ እርጉዝ ሴት በፀብ እና አደገኛ ዕፅ በመጠቀሟ ካሊፎርኒያ እስር ቤት ትገባለች፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ትወልዳለች ተብሎ ከሚጠበቅበት 3 ወር ቀደም ብላ በብረት በተከረቸመው የእስር ቤት ወለል ላይ ወልዳ ትገኛለች፡፡ የእስር ቤቱ ጠባቂ ፖሊሶች ሲደርሱ የተወለደው ህፃን መተንፈስ አቁሞ ነበር፡፡ አትሙት ያለው ነፍስ ግን በስልክ ተደውለው በተጠሩ የህክምና ባለሙያዎች እንክብካቤ ከሞት ሊተርፍ ችሏል፡፡

 

  1. የኢሜሬትስ አውሮፕላን ሽንት ቤት ውስጥ የተወለደ ህፃን

 

በዓለማችን ላይ ታዋቂ የሆነው ኢሜሬትስ አየር መንገድ ከዱባይ ወደ ማኒላ በሚያደርገው በረራ ላይ ፍሊፒን የተባለች ሴት በድንገት ባጋጠማት ምጥ አውሮኘላኑ ሽንት ቤቱ ውስጥ ሴት ልጅ ልትወልድ ችላለች፡፡ ህፃኗ “ኤኬ” የሚል ስም የወጣላት ሲሆን ይህም የኢሚሬትስ በረራ ኮድ ነበር፡፡ ኤኬ ከተወለደች በኋላ አውሮፕላኑ በድንገት እንዲያርፍ ቢገደድም በበረራ ወቅት እናትና ልጅን የአውሮፕላኑ  ሊድ ላይት ሲያሞቃቸውና የኦክሲጅን ማክሱንም ሲጠቀሙ ነበር፡፡

 

  1. የእንግሊዝ ወታደር በአፍጋኒስታን ወለደች

 

በእንግሊዝ ታሪክ ውስጥ በጦርነት ወቅት ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው፡፡ ጠመንጃ ታጣቂዋ እናት የሚያስገርመው እርጉዝ መሆኗን እርሷ እርሷ የማታውቅ ሲሆን ዶክተር ያያት ምጥ ይዟት ለህክምና ስትቀርብ ብቻ ነው፡፡ የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስቴር እርጉዝ መሆኗ ቢታወቅ ኖሮ ወደ ጦርነት እንድትሄድ የሚያስገድዳት ማንም እንደሌለ ገልጿል፡፡ 

  1. 250 ኪ.ግ የምትመዝነው ሴት የገጠማት ምጥ

 በሮማኒያ የምትኖር የ25 ዓመት ወጣት ናት፡፡ ይህች ወጣት 250 ኪ.ግ ስትመዝን የመጀመሪያ ሴት ልጇን ወፋፍራም ሰዎችን ለማከም በተገነባ ሆስፒታል ውስጥ በሠላም ተገላግላለች፡፡ 2.9 ኪ.ግ የሚመዝነው ህፃን የ70 ኪ.ግ ባሌ እና የእኔ ፍሬ ነው ስትል ለጋዜጠኞች ተናግራለች፡፡ እሷን ወደ ሆስፒታል ለመውሠድ የ3 አምቡላንስ ሠራተኞች እና የእሣት አደጋ ሠዎች ተረባርበዋል፡፡

Social & newsletter

Search