Lifestyle

ሎሚ: በዓለም ላይ ተወዳጅና ተመራጭ ፍራፍሬ ጥቅሞች

አሁን አሁን የሎሚ መዓዛ ያላቸው ምግባች ተመራጭ እየሆኑ በመምጣታቸው ሎሚን በዓለም ላይ ተወዳጅና ተመራጭ ፍራፍሬ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሎሚ የበቀለበት ሀገር በትክክል ባይታወቅም ብዙዎች የሚስማሙበት ግን ከህንድ፣ ደቡባዊ በርግ እና ከቻይና ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡

ከአንድ መካከለኛ ሎሚ ስድስት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂን ማግኘት እንችላለን፡፡ ለዚህም መጠኑ ተለቅ ያለ፣ ሲነካ የሚጠነክር፣ የበሰለ /ቢጫ ቀለም ያለው/ እና ስናሸተው ጥሩ የሎሚ መዓዛ ያለውን ሎሚ በእጃችን እየተጫንን ጠንካራ ነገር ላይ ማሸት ወይም በማይክሮ ዌቭ (microwave) ለ30 ሰከንድ ማቆየት የተፈለገውን መጠን ማግኘት ይቻላል፡፡

የሎሚ ጥቅሞች

 1. ለጥርስ ውበት እና እንክብካቤ
  • ጥርሳችንን በሚያመን ወቅት ህመሙን ለማስተገስ ይረዳል፡፡
  • ድድ በሚደማበት ጊዜ ሎሚ ቆርጦ ማሸት ደሙ እንዲቆም ይረዳል፡፡
  • መጥፎ የአፍ ጠረን ለማስወገድ በሎሚ ውሃ መጉመጥመጥ
  • ጥርስን ለማፅዳት እና እንዲጠነክር ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሎሚ ያላቸው የጥርስ ሳሙናዎችን ወይም ያለን የጥርስ ሳሙና ላይ ሎሚ ጨምሮ መጠቀም፡፡
 2. ለቆዳ ውበት
  • ከእርጅና ጋር ተያይዞ የሚመጡትን የቆዳ መሸብሸብን በማስቀረት በራስ መተማመናችንን ከፍ ያደርጋል፡፡
  • በቆዳ ላይ የሚገኝ ጠባሳን ለማጥፋት ሎሚ የጐላ ጥቅም አለው፡፡
  • የደረቀ ቆዳን ለማለስለስ ሎሚ ጨምቆ ከግሪሲሊን ጋር በመቀላቀል መቀባት
  • በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳን በማቀዝቀዝ እንዳይጐዳ ይረዳል፡፡ ስለዚህ ሎሚን የያዙ ሳሙናዎችን መጠቀም ይመከራል፡፡
  • ሎሚ መቀባት የወባ ትንኝ እንዳትቀርበን ያደርጋል፡፡
  • በአንዳንድ ነፋሳት እንደ ንብና የወባ ትንኝ በምንነደፍበት ጊዜ መርዛቸውን ለማስወገድ እና ህመሙን ለማስታገስ ሎሚ መቀባት ይጠቅማል፡፡
  • የሎሚ ጭማቂ የወጣውን ቡግር ከማድረቅ አልፎ ሌላ እንዳይወጣ ይከላከላል፡፡
 3. ለፀጉር ውበት
  • ፀጉርን ለማለስለስ እና አብረቅራቂ በማድረግ ውበት ለማላበስ የሎሚ ጭማቂ መጠቀም፡፡
  • የሎሚውን ልጣጭ ፀሐይ ላይ አድርቆ በመውቀጥ ፀጉራችንን ከመታጠባችን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት መጠቀም ራስ ምታትን ከማስወገዱ በተጨማሪ ሰውነታችንን ያቀዘቅዛል፡፡
  • የሎሚ ጭማቂ ለፎሮፎር፣ ለሚነቃቀል ፀጉር እና እንደሁም ሌሎች ከፀጉር እና ከራስ ቅል ጋር የተያያዘ ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
  • የፀጉር ቀለምና ማስለቀቂያዎች በምንጠቀምበት ወቅት ቆዳችን እንዳይጐዳ ያደርጋል፡፡
 4. የሰውነት መፍጫ (digestive system) አካላት
  • የሎሚ ጭማቂ ለሆድ ድርቀት እና ለስቅታ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡
  • በየቀኑ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ሆድ እና ጉበት ውስጥ ያለን ቆሻሻ ለማስወገድ ይረዳል፡፡
  • የሎሚ ጭማቂ ከወይራ ዘይት ጋር መጠጣት የሀሞት ጠጠርን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ለኩላሊት ጠጠር ተመራጭ ነው፡፡
  • ጥቂት የሎሚ ጭማቂ ከሞቀ ውሃ ጋር መውሰድ የምግብ አለመፈጨት ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ማግሳት፣ ሆድ መንፋት እና ማቃጠል የመሳሰሉ ስሜቶችን ያስቀርልናል፡፡

ብዙ ሀሞት እንደመረት በማድረግ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡ ስለዚህ ከበድ ያለ ምግብ ከተመገብን በኋላ ማዘዝ ያለብን የሎሚ ውሃ በጨው ወይም እንዳይመረን በማር ወይም በስኳር መሆን አለበት፡፡

image
image
 1. የሰውነት ክብደት ለመቀነስ
  • ጠዋት ጠዋት የሎሚ ውና ከጨው ወይንም ከማር፣ ከስኳር ጋር በመቀላቀል መጠጣት በሰውነት ውስጥ ተከማችቶ የሚገኝ ኮሌትስሮል /ስብ/ በፍጥነት እንዲቀንስ በማድረግ አላስፈላጊ ክብደትን አስወግዶ ጤናችንን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
 2. ለመተንፈሻ አካላት በሽታዎች
  • በጉንፋን ከመያዛችን በፊትም ሆነ ከተያዝን በኋላ የሎሚ መጠጣት በቶሎ እንድንድን ይረዳል፡፡
  • አስምን ጨምሮ ሌሎች ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተገናኙ በሽታዎችን ለማዳን ይረዳል፡፡
 3. ለኢንፌክሽን
  • ለቶንሲል፣ ቃር እና ሌሎች የጉሮሮ ኢንፌክሽኖችን ለማዳን በየቀኑ በነጭ ሽንኩርት ሎሚ ውሃ መጉመጥመጥ ቁስሉን ከማጠብ በተጨማሪ ባክቴሪያዎችን ይገድላል፡፡
  • የመሽኛ አካላት ኢንፌክሽን ለማከም እና ለመከላከል ይረዳል፡፡
 4. እግርን ለብ ያለ የሎሚ ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ እግራችን ዘና እንዲል እና እንዳይሸት ያደርጋል፡፡
 5. የደም ግፊትን ለመቆጣጠር
  • ለደም ግፊት የሎሚ ውሃ መጠጣት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ምክንያቱም በውስጡ ፖታሲየም የተባለ ማእድን ስለያዘ የሰውነት ፈሳሽ ይዘቶችን የተመጣጠነ በማድረግ የልብ ምትንና የደም ግፊትን ይቆጣጠራል፡፡
 6. ሎሚ አዕምሮን ለማዝናናት ስለሚረዳ ለድብረት፣ ለጭንቀት እና ለማቅለሽለሽ ተመራጭ ነው፡፡ ስለዚህ በመኪና በምንጓዝበትም ወቅት ሎሚ በማሽተት እና በማሽተት የማቅለሽለሽ ስሜት መቀነስ ይቻላል፡፡
 7. ለትኩሳት
  • የሎሚ ውሃ መጠጣት ሰውነታችንን እንዲያልበው በማድረግ ያቀዘቅዛልና፡፡
 8. ሰውነታችን ፈሳሽ በሚያንሰው ጊዜ ለምሳሌ በሚያስቀምጠን ጊዜ የሎሚ ፈሳሽ የጎደለውን በመተካት አቅም ይሰጠናል፡፡
 9. ካንሰር ለመከላከል ሎሚ በውስጡ ፍላቪኖይድ (Flavinoid anti-odidant) ስላለው ሰውነታችንን ከካንሰር ይከላከላል፡፡
 10. በሽታ የመከላከል አቅማችንን ይጨምራል፡፡ ሎሚ በውስጡ ሲትሪክ አሲድ (Citric acid) ስለያዘ ነጭ የደም ህዋሶችን (WBC’s) አና አንቲቦዲ (Antibody) እንዲመረቱ በማድረግ በሽታ ይከላከላል፡፡
 11. መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ
  • እጃችንን እንዲሁም የኩሽና እቃዎችን እንደ መጥበሻ፣ ማንቆርቆሪያ የመሳሰሉትን ከማጠባችን በፊት ሎሚን ቆርጦ በመቀባት አላስፈላጊ ጠረንን ማስቀረት ይቻላል፡፡
  • የተጠቀምናቸውን ሎሚዎች ቆሻሻ የምናጠራቅምበት ቦታ አካባቢ ማድረግ አካባቢው በሎሚ መአዛ እንዲያውድ በማድረግ መጥፎ ሽታን ያስወግዳል፡፡

ታዲያ አንድ ሎሚ ለራስዎት … አንድ ሎሚ ለወዳጆት !ዛሬውኑ  ይሞክሩ …!

I believe that a simple and unassuming manner of life is best for everyone, best both for the body and the mind.

Albert Einstein

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and typesetting industry. Lorem Ipsum has been the industry's standard dummy text ever since the 1500s, when an unknown printer took a galley of type and scrambled it to make a type specimen book. It has survived not only five centuries, but also the leap into electronic typesetting, remaining essentially unchanged. It was popularised in the 1960s with the release of Letraset sheets containing Lorem Ipsum passages, and more recently with desktop publishing software like Aldus PageMaker including versions of Lorem.

Social & newsletter

Search