Lifestyle

ዊትኒ ሁስተን: The Rise and Fall of Black Star

ቅዳሜ የካቲት 11/2012 ጠዋት ነበር እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር አንድ በሎስ አንጀለሰ በሚገኝ ትልቅ ሆቴል የሚሠራ ሠራተኛ ነው፡፡ እንደዚሁ ቀደሙ የሆቴሉን ደንበኞች ማረፊያ ለመጐብኘት እና ለመቆጣጠር ክፍል ቁጥር 434 ይገባል፡፡ ድምፅ በማጣቱ ደንበኛቸው ለስራ ጉዳይ እንደወጣ እና ሆቴሉን ለማፅዳት ምቹ ጊዜ መሆኑን ይገምታል፡፡ “ሄሎ ሠር” እያለ ቢደጋጋምም መልስ አልተመለሠለትም፡፡ ከፍቶ ሲገባ አልጋው ተተኝቶብኛል ብሎ ለማሣለቅ ይመስላል ዝብርቅርቅ ብሎአል፡፡ ጠረጴዛውም ቢሆን በቁሣቁሶች ተሞለቶአል፡፡ ይህ ለአንድ ሱፐርቫይዘር የተለመደ የቀን ተቀን ልምምድ ስለሆነ ብዙም አላስደነቀውም፡፡ ተረኛ የነበረችውን አልጋ አንጣፊ በያዘው ትልቅ የሆቴሉ ስልክ መፅዳት አንዳለበት ደውሎ በመናገር ከሆቴሉ በመጣበት እግሩ ተመልሶ ይወጣል፡፡ የፈረደባት የፅዳት ሠራተኛ ግን የተወዳጇን ጥቁር ልዕልት መሞት ለማየት ቀዳሚ ነበረች፡፡ የሚተኛበትን አልጋ በማዕረግ ካነጠፈች በኋላ ወደ መታጠቢያው ክፍል ስትገባ ጥቁሯ ኮከብ መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ተዘፍቃ ታያታለች፡፡ በድንጋጤ እንዴት ከዛ ክፍል እንዴት እንደወጣች አታውቀውም ብቻ ለድንገተኛ አደጋ ተብሎ የተሠቀለው የኮሪደር ስልክ ጋር እራሷን ታገኘዋለች፡፡ የሚገርመው እዛው ቆማ ማስደወል የሚያስችላት ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጇ መያዟ ነበር፡፡ ምን አስሩጦ ከክፍሉ አስወጣት! የደወለችው በኮሪደር ስልክ ወደ ሎቢው (እንግዳ መቀበያው) ነበርና ሱፐርቫይዘሩ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በመሆን ሲንደረደሩ 434 ይመጣሉ፡፡ ከገንዳው አውጥተው ህይወቷን ለማትረፍ ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡ ይሄኔ 911 በመደወል ድንገተኛ እርዳታ ይጠይቃሉ፡፡ ነገሩን የጦዘው እና ሁሉንም በድንጋጤ ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ያደረጋቸው ደግሞ አደጋው የደረሠው ከማንም ይልቅ የሚወዷት እና ታዋቂ አቀኝቃኛቸው ሁስተን መሆኗን ሲያውቁ ነው፡፡ ግን ምን ያደርጋል ዘይግተው የመጡት የተካኑ ባለሙያዎች ነፍሷን ሊያድኑ ብሎም ሊመልሱ አልቻሉም፡፡ ይህ ሲሆን እንግዲህ ከቀኑ 9፡30 አካባቢ ነበር፡፡ ወዲያው ማለት ይቻላል የአሜሪካ ትላልቅ የቴሌቪዢን ጣቢያዎች ዜናውን በማቅረብ የዓለም ህዝብን ሀዘን በሀዘን አደረጉት፡፡ ሲኤንኤን፣ ፎክስ ኒውስ እና ኤም ኤስ ኤን ሞተች ከተባለበት ሰዓት አንስቶ በቀጥተ ሲዘግቡ ነበር፡፡

       ዋትኒ ኤልሣቤዝ ሁስተን እ.ኤ.አ 1963 ነሐሴ 9 በኒውጀርሲዋ የድሃ መንደር ኒዋርክ የተወለደች ሲሆን በማቀንቀን፣ በመተወን፣ በሞዴሊንግ፣ ፊልም በማዘጋጀት፣ ቅጂ በማዘጋጀት እና በዘፈን ግጥም ፀሐፊነቷ ትታወቃለች፡፡ እርግጥ ብዙዎቻችን በዚህ ሁሉ ታለንቷ ሣይሆን በሚሠረቀረቀው ድምፅ እና ዘ ቦዲ ጋርድ በሚለው ፊልም ላይ ባሣየችው ድንቅ ብቃት ነው የምናውቃት ይህቺ ሴት ጥቁሩም ነጩም አሜሪካዊ እንደ ጣዎት ያመልካታል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በተለያየ ጊዜ አና በተለያዩ ዘፈኖቿ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡ ለመሆኑ በ54ኛው የግራሚ አዋርድ ላይ ተጋባዥ አቀንቃኝ የነበረችው ዊትኒ ኤልሣቤዝ ሁስተን ማን ነች? ለዝግጅቱ አንድ ቀን ሲቀረው ለምንስ ሞተ ተገኘች ከዚህ በታች በጥቂቱ የጥቁሯን ኮከብ ህይወት ታሪክ ይዘን ቀርበናል ተከታተሉን፡፡

ዊትኒ ከ1963-1976

የቤተክርስቲያን ዘማሪ ከሆኑት እናቷ ሲሲ ሁስተን እና የጦር ሰራዊት አባል ከነበሩት አባቷ ጃን ሩሴል ሁስተን ሁለተኛ ልጅ ሆና ወደምድር የመጣችው ጥቁሯ ዊትኒ በቅርብ ዘመዶቿ ማለትም አጐቷ አሪታ ፍራንክሊን እና በእናቷ የዝማሬ ጥበብ ተፅአኖ ውስጥ ማደግ ግድ ብሎአት ነበር፡፡ ይህ ተፅዕኖ ለዝና እና ለብልፅግና የሚያበቃ ነው፣ ብዙዎችም ፈልገው አይገኙትም፡፡ ዊትኒ ገና በ8 እና በ9 ዓመቷ አጐቷ ፍራንክሊን የሙዚቃ ስቱዲዮ መሄድ ታዘወትር ነበር፡፡ አስራ አንድ አመት ሲሆናት የእናቷን እግር በመከተል በኒው ሆኘ በኘቲስት ቤ/ክርስቲያን የሶሎ ዘማሪ በመሆን የሙያ ጉዞዋን አንድ ብላ ጀመረች፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በዚህ እድሜዋ ፒያኖ በሚገባ መጫወት ትችል ነበር፡፡

ዊትኒ 1977-1984

ይህ ዘመን ዊትኒ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት የተንደረደረችበት የአፍላነት እድሜ ነው፡፡ እናቷን ተከትላ በመሄድ ታቀነቅንበት በነበረው የምሽት ክለቦች ትቆይ ነበር፡፡ የኃላ ኃላ የክበቡን መድረክን በመያዝ በአስራ አራት አመቷ በሚቼል ዛገር ባንድ አጃቢ ሙዚቀኛ ሆነች፡፡ በጊዜው ታዋቂ የነበረው የቻካ ካሃን ዘፈንን በማጀብ ወደ ታዋቂዎች ጎራ ለመቀላቀል ማንኳኳት ጀመረች፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከሚስረቀረቀው ድምጿ ሌላ የፎቶ ባለሙያው ካሪንግ ሃል ካያት በኋላ ከ1980 ጀምሮ የፋሽን ሞዴል ሆና መስራቱን ተያያዘችው፡፡ በዚህም የተነሳ የመፅሔቶችን ሽፋን  ላይ በመውጣት እና የቴሌቪዢን ማስታወቂያ በመስራት በጊዜው ከነበራት እድሜ አንፃር የሠዎችን ቀልብ የምትስብ ታዳጊ ሆነች፡፡

       በወቅቱ ከብዙ የሙዚቃ አሣታሚ ኤጀንሲዎች ለዊትኒ አብረን እንስራ ጥያቄ ቢበዛም እናቷ ሲሲ ግን ልጇ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን መጨረስ እንዳለባት በማስገንዘብ ውድቅ ታደርግባቸው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ 1983 የምሽት ክበብ ከእናቷ ጋር በምታቀርበው ሙዚቃ በመደነቁ የታዋቂው አሪስታ አሣታሚ ስራ አስኪያጅ ክላቪ ዴቪስ ዊትኒን ውል ለማሰፈረም ቆርጦ ይነሣል፡፡ ኃላም ተሣክቶላት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረግ የቅጂ ውል ሊያስፈርማት ችሎአል፡፡ ዊትኒ ለአሪስታ ካምፓኒ እ.ኤ.አ 1983 ስትፈርም ወዲያው ወደ ሙዚቃ ቅጂ አልገባችም ምክንያቱም ለአስገራሚ ታለንቷ የሚሆን ትክክለኛ ባለሙያ እና መሣሪያ እስኪገኝ ድረስ ነበር፡፡

ዊትኒ 1985-1986

ይህ አመት ዊትኒ ወደ ስኬት ጫፍ የደረሰችበት እና በአለም አቀፍ ደረጃ ስራዋ ተደማጭ የሆነበት ጊዜ ነበር፡፡ በ1984 መጨረሻዎቹ ወራት የለቀቀችው ነጠላ ዜማ በቢል ቦርድ ቶኘ 5 ከሚባሉተ ውስጥ አንዱ ቢሆንም በ1986 ከወጣው “ደቦት” አልበም ጋር ሲነፃፀር ከግምት የሚገባ አይደለም፡፡ በጊዜው የወጣውን አልበም የሮሊንግ ስቶን መጽሔት የዓመቱ አስደናቂ ድምፅ ሲለው፣ የኒወርኩ ታይም ደግሞ “አስደናቂ እና የተለየ የድምፅ ትዕይንት” ነው ብለው ነበር፡፡ በአውሮፓ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ተደማጭነቱን በማስፋት ቁጥር አንድነቱን ቢያስመሰክርም በአንዳንድ ሀገራት ብዙም ቦታ አልተሠጠውም፡፡ በመቀጠል “Saving all my love for you” የተባለው ነጠላ ዘፈኗ ግን የትም ቢሄዱ በጊዜው ቁጥር አንድነቱን የተፎካከረው አልነበረም፡፡ በ19 ሰማኒያዎቹ ኤምቲቪ የነጭ ዘፈኖችን ብቻ በማቅረቡ ከብዙዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እና ወቀሣ ይደርስበታል፡፡ ይህን እያስተባበለ ቢቆይም የዊትኒ ዘፈን ሲመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁር ሴት ዘፈንን እያደጋገመ በማቅረብ የነበረውን ልማድ ታሪክ ማድረግ ችሎአል፡፡ በአር ኤንድ ቢ ዘርፍ ከሁለት መቶ ዘፈኖች ቁጥር አንድ ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የሚያስገርመው ለ14 ተከታታየይ ሣምንታት ቢልቦርድ ሠንጠረዥ እናት ላይ ቆየ፡፡ በመላው አለምም ላይ 25 ሚሊዮን ቅጂዎችን በመሸጥ በ1986 የግራሚ ሽልማት በሶስት የተለያዩ ዘፈኖች አሸናፊ ሆነ፡፡ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የምታሣየው የግል ብቃትም ተፈጥሮዋን ተመኝተው ብዙዎች እንዲቀኑባት አድርጐአል፡፡ እንደውም በሙዚቃ አዋቂዎች የዊትኒ ብቃት ለብዙ ጥቁር ሴት አቀንቃኞች ምሣሌ የሚሆን እና በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡ እንደ ጄኔት ጃክሠን እና አኒታ ቤከርን የመሣሠሉ እንስቶች እግሯን ተከትለው እንዲወጡ ምክንያት ነበረች፡፡

 

ዊትኒ 1987-1991

 

እ.ኤ.አ 1987 ዊትኒ ሁለተኛ አልበሟን ለገበያ ያቀረበች ሲሆን መጀመሪያ ከተለቀቀው አልበም ጋር ይመሳሰላል ተብሎ አስተያየት የተሠጠበተ ነበር፡፡ እርግጥ በሽያጭ ደረጃ አሁንም ስኬትማ አልበም በመሆን በተለያዩ ሀገራት የመጀመሪያ ደረጃን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ በዓለም ላይ 20 ሚሊዮን ቅጂዎች ሲሸጡ በ1983 በተደረገው የግራሚ አዋርድ አዋርድ በሶስት ዘሮፎች በድጋሚ ታጭታ አንዱን ብቻ አሸንፋለች፡፡ የአሜሪካ ሙዚቃ አዋርድን ሁለት ተከታታይ አመቶች ስትወስድ ሶል ትሬን ሙዩዚክ አዋርድንም አግኝታለች፡፡ ታዋቂው የፎርከስ መጽሔት ባወጣው ታዋቂ አፍሪካ አሜሪካዊ የጥበብ ሠዎች መካከል ከቢል ኮዝቢ፣ እና ከኤዲ መርፊ በመቀጠል ሶሰተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

       ዊትኒ ከሙዚቃው ባለፈ የፀረ አፖርታይድ እንቅስቃሴ በተለይም የማንዴላ ደጋፊ ነበረች፡፡ ይህንንም ድጋፉን ከማንኛውም አፖርታየድ ደጋፊ ኤጀንሲ ጋር አብራ መስራትን እንቢ በማለት አሣይታለች፡፡ እ.ኤ.አ 1988 የጥቁር ጀግና ኔልሰን ማንዴል 70ኛ የልደት በዓል ሲካሄድ በእንግሊዙ ዊንብሌይ እስታዲየም 72000 ሰዎች በተገኙበት አቀንቅናለች፡፡ ለፀረ አፖርታይድ ኔግሮ ኮሌጅም ማሰሪያ   የሚያስፈልገውን ገንዘብ በማሠባሰብ ቀዳሚ ሚና ተጫውታለች፡፡

       የዊትኒ ሁስተን የህፃናት ፋውንዴሽንም እ.ኤ.አ 1989 ስታቋቁም በዓለም ላይ ለሚገኙ የተቸገሩ ህፃናት መረጃ የሚሆን ብዙ ገንዘብ በማሠባሠብ ጐዳና የወደቁ ህፃናትን እና በተለያዩ በሽታዎች የተጎዱ ህፃናትን ትረዳ ነበር፡፡

 

image
image

 ዊትኒ እና የፊልም ስራዎቿ

 እ.ኤ.አ ከ1992 በፊት ከሮበርት ዲነሮ፣ ኪወንስ ጆንስ እና ስፖይክ ሊ ጋር በመሆን ፊልም እንድትሠራ ብትጋበዝም ለመሣተፍ ከነበራት ቀዝቃዛ ስሜት የተነሣ ቀርቶ ነበር፡፡ ኋላ ግን በ1992 ከኤቫን ኮስተር ጋር ሆነ የሠራችበት ዘ ቦዲ ጋርድ የተሰኘው ፊልም የብዙዎች አፍ ውስጥ እንድትገባ አድርጐአል፡፡ የአሜሪካው “USA Today” በ2007 ላይ ባደረገው ምርጫ ባለፉት 25 አመታት ውስጥ ተጠቃሽ ከሆኑት 25 ፊልሞች ውስጥ ነበር፡፡ የሚገርመው ዊትኒ በዚህ ፊልም ከራዚ አዋርድ መጥፎ ተዋናይ የሚለውን ዘርፍ አሸንፋለች፡፡ ይህም ዊትኒ እራሷን እንጂ ሌላን መስላ መጫወተ ባለመቻሏ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ወቀሣ ሣያደናቅፈው ቦክስ ኦፊስ ውስጥ ትልቅ ስኬት አግኝቶአል፡፡ በገቢም ቢሆን በዓለም ላይ 410 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማስገባት ተሣክቶለታል፡፡

በዚህ ፊልም ውስጥ የነበረው ማጀቢያ ሙዚቃ “I will always love you” በዓለም ላይ ስኬትማ ከሚባሉ ነጠላ ዜማዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እ.ኤ.አ 1974 ይህን ዘፈን ዶሊ ፓርተን ብትጫወተውም በ”RIAA” ታሪክ 4 ኘላቲኒየም ሽልማቶችን ያገኘው ዊትኒ ስትጫወተው ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በቢልቦርድ ሠንጠረዥ ከመቶ ዜማዎች ውስጥ አንደኛ፣ በዓለም ላይ 12 ሚሊዮን ኮፒዎችን በመሸጠጥ ተወዳጅነቱን አስመስክሮአል፡፡

እ.ኤ.አ 1995 ደግሞ ከእነ አንጀል ባሴት፣ ሌሬት ዲቫይን እና ሌና ፎቸን ጋር በመሆን “ waiting to Exhale” የሚባለው ፊልም ተጫወታለች፡፡ ይህ ፊልም ካለአራት እንስት አፍሪካ አሜሪካውያን ሰዎች በትዳር ውስጥ ትግል የሚያሣዩ ነበር፡፡ ዊትኒ የባቫና ጃክሠን ባህሪ ወክላ ስትጫወት ብዙዎች ጥቁር ኘሮፌሽናል ሴቶች እናትም ሆነው መስራተ እንደሚችሉ የሚያሣይ ነው ብለዋል፡፡ በመቀጠል 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተከፍሎአት “The Biships wife” የሚለው ሠርታለች፡፡ በዚህ ፊልምም ከፍተኛ ስኬት እና እውቅናን አግኝታለች፡፡ ሲንደሬላ እና “Fairy god Mother” የተባሉ ፊልሞችም ዊትኒ የውስጥ እምቅ ችሎታዋን ለሌሎች የገለጠችባቸው ነበሩ፡፡

የዊትኒ ግላዊ ህይወት

በ1980ዎቹ ዊትኒ ከአሜሪካ የፉትቦል ተጫዋች ራንዳል ካኒጋሃም እና ከፊልም አክተር ኤዲ መርፌ ጋና የፍቅር ግንኙነት ጀምራ እንደነበር ይነገራል፡፡ ከእነሱ በኋላ የአር ኤንድ አቀንቃኝ ከሆነው ቦቢ ብራውን ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ለሶስት ዓመት ከቆየች በኋላ ጆላይ 18/1992 ተጋብተዋል፡፡ ከአመት በኋላ ቦቢ ክርስቲና ብራውን የምትባል ሴት ልጅን ወልዳለች፡፡

I believe that a simple and unassuming manner of life is best for everyone, best both for the body and the mind.

Albert Einstein

Social & newsletter

Search