News

ሽንኩርት ሲልጡ ለምን ያለቅሳሉ ?

አንዳንዶች ሽንኩርት ሲልጡና ሲከትፉ ምንም አይነት ስሜት አይሰማቸውም በአንፃሩ ሌሎች ደግሞ ያነባሉ፡፡ ሽንኩርት በሚከትፉበት ወቅት በሽንኩርት ሴል ውስጥ የሚገኙ ኢንዛይሞች (Enzymes) ከተለያዩ ኬሚካሎች ጋር ሲደባለቁ ጋዝ ይፈጠራል ይህ ጋዝ በአይን ውስጥ በሚገባበት ወቅት ሰልፈሪዩክ አሲድ (H2SO4) ይፈጥራል የዚህ አሲድ በአይን ውስጥ መፈጠር ደግሞ ለማቃጠሉ ለመቆጥቆጥና ለማስለቀስ ዋንኛ ምክንያት ነው፡፡ ታዲያ ሽንኩርት እንዴት አንዳንዶችን ሲያስለቅስ ሌሎችን ምንም አያደርጋቸውም ለሚለው ጥያቄ በዊስከንሳን ማድስን የ Horticulture ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አርዊን ጎልድመን ሲመልሱ ምናልባት የአይናችን ኬሚስትሪ የተለያየ ሲሆንና ለሰልፈሪክ አሲድ የሚኖርን ምላሽም ከሰው ሰው ሊለያዩ እንደሚችል ጠቁመው አንዳንዶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መቆጥቆጥና ማስለቀስን ሲፈጥር ሌሎች ደግሞ ይህንን አሲድ የመቌቌም ብቃት ስላላቸው ምንም አይነት ሁኔታ እንደማይፈጠርላቸው ገልፀዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍም ዶ/ር ጎልድማን እንደሚሉት ሽንኩርቶቹ ከመከተፋቸው በፊት በደንብ ማቀዝቀዝ የኢንዛይሞችን የመልቀቅ ሂደት ስለሚያዘገየው ችግሮቹንም በተወሰነ መልኩ ይቀንሰዋል፡፡ ባለሞያው አያዘውም ከላይ ከቀጭኑ ጫፍ በኩል መላጥና መክተፍ መጀመር ሌላው አማራጭ መሆኑን ገልፀው እነዚህ ኢንዛይሞች በብዛት የሚገኙት በወፍራሙ ጫፍ በኩል በመሆኑ ይህንን ማድረጉ ችግሩን በተወሰነ መልኩ ያቃልለዋል ብለዋል አንዳንዶች ሽንኩርትን ለመክተፍ በጣም የተሳለ ቢላዋን መጠቀም ሴሎቹ እንዳይጎዱና ኢንዛይሞችን እንዳይለቁ ስለሚያደርጋቸው ጥሩ መፍትሔ እንደሆነ ይጠቁማሉ በተጨማሪም በውሃ ውስጥ ሽንኩርትን መክተፍ የሚለቀቀውን ጋዝ ለማፈን ስለሚረዳ ማስለቀሱን እንደሚቀንስ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ፡፡

image
image

Social & newsletter

Search