Medical

የሚጥል በሽታ (Epilepsy)

የሚጥል በሽታ በአገራችን ያለው ስርጭት በውል ባይታወቅም ከሚገመተው በላይ መሆኑ አያጠራጥርም ምክንያቱም ብዙዎች የዚህ በሽታ ተጠቂዎች ወደህክምና ከመምጣት ይልቅ ወደባህላዊ ህክምና ስለሚያዘነብል ትክክለኛ ስርጭት መግለፅ ያዳግታል፡፡ በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል በሽታው ከሠጥጣንና ተዛማች ነገር ጋር ስለሚያያዘ ጭራሽኑ ሀኪም እንዳያያቸው ያደርጋል፡፡

ሀ/ ትርጉም (definition)

 1. ሲዝር (Seizure or convulsion) ማለት ህሊናን አስቶም ሆነ ሣያስት ጡንቻን በማንቀጥቀጥም ሆነ ድንገት ፀጥ በማድረግ በከፊልም ሆነ በመላ አካል ላይ የሚገለፅ የመጀመሪያው ማንቀጥቀጥ ነው፡፡
 2. convulsionማለት ጡንቻን በማንቀጥቀጥ ብቻ በከፊልም ሆነ በመላ አካል ላይ የሚገለፀው ማለት ነው፡፡
 3. ኤፒለኘሲ (Epilepsy) ማለት ምክንያቱ በውል ያልታወቀ በተለያየ ጊዜ ተደጋግሞ የሚከሠት ማንቀጥቀጥ ነው፡፡

ለ/   አፍላቶች ማንቀጥቀጥ በብዙ መልኩ ሊገለጥ ይችላል፡፡ ይሔንንም መንቀጥቀጥ በብዙ መልኩ መልሱ ሊከፋፈል ይችላል፡፡

 1. ከፊል ማንቀጥቀጥ ማለት የተወሰነ የአካልን ክፍል ብቻ በማንቀጥቀጥ የሚገለፅ ነው፡፡
 1. ሀ. ቀላል ከፊል ማንቀጥቀጥ ይህ አይነቱ ማንቀጥቀጥ ህሊናን ሳያስት የስሜት ህዋሣትን በመቀያየር ወይም አስተሣሰብን በማዛባት የሚገለፅ ነው፡፡
 2. ለ. የተመሳበበ ከፊል ማንቀጥቀጥ ይህ እውነቱን ማንቀጥቀጥ ህሊናን አስቶ ጡንቻ የስሜት ህዋሣትን በመቀያየር ወደ አስተሣሰብ በማዛባት የሚገለጽ ነው፡፡ ይሄኛው አይነት ማንቀጥቀጥ ከመከሠቱ በፊት በተለዩ መንፈሳዊ ስሜት (Aura)
 1. መላ ማንቆጥቆጥ ይህ አይነቱ ማንቀቆጥቆጥ እንደ ከፊል ማንቆጥቆጥ እንደ ከፊል ማንቀጥቀጥ ሁሉ በጡንቻ ወይመ የስሜት ህዋሣትን በመቀያየር የሚገለፅ ሲሆን ልዩነቱ በመላ አካል መሠራጨቱና ህሊናንም በማሳት መጋለጥ ነው፡፡ ይህም በሁለት ዋና ዋና አይነቶች ይከፈላል፡፡
 1. ሀ. ድንገት ፀጥ ማለት በሽተኛው በጥቂት ሠከንዶች ምናልባትም ከአንድ ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ያህል ህመምተኛው ላለበት ሁኔታ ሳይወድቅ ወይመ ሳያንቀጠቅጠው ፀጥ ይልና በድንገት ወደነበረበት ቦታ ይመለሣል፡፡ ይህ አይነቱ ብዙ ጊዜ የሚከሠተው /የሚጀምረው/ በልጅነት ዕድሜው ነው፡፡ /ከ4-8 ዓመት/ አገላለፁም በድንገት ፀጥ ወይም ህሊናን መሣት ስለሆነ ሰዎች የቀን ቅዠት ይሉታል፡፡
 2. ለ. መላ ጡንቻን ማንቀጥቀጥ (Generalized tonic-clonic) ይህ አይነቱ ማንቀጥቀጥ አብዛኛው ሰው የሚያቀው ሲሆን ህመምተኛው ጩኸት ካሠማ በኋላ ባለበት ይወድቅና የመንፈራፈር ሁኔታ ሲታይበት ምራቅ መድፈቅ፣ ሽንት ወይም ሠገራ የመሳት ምላስን በጥርስ አማካኘነት የመጉዳት ሁኔታ ሊገለፅ ይችላል፡፡
 3. ሐ. በከፊል የሚጀመር መላ ማንቀጥቀጥ ይህ አይነቱ ማንቀጥቀጥ በግማሽ አካል ላይ ይጀምርና /እግር፣ እጅ፣ ፊት…. ላይ/ ከዚያ በኋላ መላ አካላት በማዳረስ የማገለፅ ነው፡፡ ህሊናን ያስታል ምራቀ ያስደፍቃል፣ ሽንት ነያስታል ከሚከባሉ በፊት የተለያዩ መንፈሶች ይታያለ እነሡም፡-
  • የተቃጠለ ጐማ መሽተት ሊሆን ይችላል
  • ጋዝ ጋዝ መሽተት ሊሆን ይችላል
  • የተለያዩ ድምፅ መስማት ሊሆን ይችላል
  • የፍርሃት ስሜት ሊሆን ይችላል
  • ትልቅ ነገር ትንሽ ሆነብኝ ሊል ይችላል
  • ትንሹ ነገር ትልቅ ሆነብኝ ሊል ይችላል

ይህ አይነቱ ማንቀጥቀጥ (Seizure) ከመላ ማንቆጥቀጥ ተለይቶ መታወቅ አለበት ምክንየቱም መንሴው ሊቆም ይችላልና ነገር ግን አስታማሚዎች ወይም ቤተሰጡ ብዙ ጊዜ ከግማሽ አካል መጀመሩን ሲያስተውል ይቀሩና ከሀኪሙ ጋር አለመግባባት ይፈጠራል፡፡ ስለዝህ አንዱን ሰው ሲያንቀጠቅጠው ከተመለሰበት አጀማመሩን በከፊል ጀምሮ መላውን ሰውነቱን ነው ያንቀጠቀጠው ብሎ ማየትና ግንዛቤን መያዝ ተጋቤና ለሀኪሙም ትልቅ መረጃ ይሆናል፡፡

image
image

ሐ. መንሴዎች

     የማንቀጥቀጥ መንሴዎች ብዙ ናቸው በእድሜ ደረጃ ሊለያይ ይችላል፡፡ ነገር ግን በዘር ወደ ዘር ወይም ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ አለመሆኑን ግንዛቤ መውሰድ ተጋቢ የሆናል፡፡ ከእርግማን ወይም ከሠይጣን ጋር ማገናኘት ስህተት የሆናል፡፡

 1. ከአንድ ወር እድሜ በታች ላሉ
  • ሲወለዱ መታፈን
  • ሲወለዱ የሚፈጠር ጉዳት ምሣሌ ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ
  • የማጅራት ገትር
  • የደም ውስጥ ስኳር ወይም ግሊኮስ ማነስ
  • በደም ውስጥ የንጥረ ነገሮች ማነስ
 2. ከአንድ ወር እስከ 12 ዓመት
  • ከፍተኛ ትኩሣት ተከትሎ ማመጣ ማንቀጥቀጥ
  • ማጅራት ገትር
  • የአንጐል ምርቀዛ
  • በተፈጥሮ የአንጐል ስሪ መዛባት
  • የጭንቅላት ጉዳት
  • ምክንያቱ ላይታወቅ ይችላል
 3. ከ12-18 አመት
  • የጭንቅላት ጉዳት
  • ማጅራት ገትር፣ የአንጐል ምርቀዛ
  • አልፎ አልፎ የጭንቅላት እጢዎች
  • መንሴው ያልቃወቁ
 4. ከ18-35 ዓመት
  • የጭንቅላት ጉዳት
  • በድንገት አልኮል መጠጥ ማቆም /ይሔ አልኮል ለብዙ ጊዜ የሚጠጡትን ይመለከታል/
  • የጭንቅላት /አንጐል/ እጢዎች
  • መንሴው ያስታወቁ (idiopathic)
  • የአንጐል ምርቆዛ ወዘተ
 5. ከ35 ዓመት ባለፍ
  • ድንገተኛ የጭንቅላት ደም ዝውውር መሠናከል (stroke)
  • የጭንቅላት እጢዎች 
  • የንጥረ ነገሮች መዛባት (metabolic disorder)

ምሣሌ፡- የኩላሊት ችግር፣ የጉበት ችግር ወዘተ

  • መንሴው ያልታወቀ (Idiopathic)

መ.  ምርመራ (Evaluation)

     የሚጥል በሽታ ያለው ሰው ሲገጥመን ማንኛውንም ግለሠብ መርዳት የምንችለው ነገር እንዳለ ማወቅ አለብን የግድ የጤና ባለሙያ መሆንን እንጠቅምም፡፡

መ. 1. ለምሣሌ፡- እያንቀጠቀጠው ከደረስን

 • ማንቀጥቀጥ ቦታ አይመርጥም ህመምተኛው ህሊናውን ስለሚስት /በተለይ 1.ለ፣ 2.ለ፣2.ሕ፣ አይነት ሲሆን/ ሲያንቀጠቅጠው ውሃ ውስጥ ሊገባ ይችላል እሳት ውስጥ ሊገባ ይችላል፣ እንዲሁም ቦታው ድንጋይ የበዛበት ወይም አስፋልት ከሆነ የአካል ጉዳት ሊደርስበት ስለሚችል ከእነዚህ አደጋዎች መከላከል በጣም አስፈላጊ እርምጃ ነው፡፡ ስለዚህ ሲያንቀጠቅጠው ቶሎ ብለን ባለበት ቦታ ላይ ብዙ ብዙ እንዳይፈራገጥ አድርገን ይዘን እስኪያልፍ መጠበቅ አለብን፡፡ ከተቻለ የተገኘውን ትራስ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ጭንቅላቱ በመሮት ጋር እንዳይጋጭ ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል በሽተኛው ምላሱን እንዳይቆርጠው አፉ ውስጥ ተጠንቅቀን /ራሳችንን ጣታችንን ሊቆርጥ ስለሚችል/ ጨርቀ ወይም እንጨት ነገር በጥርስና በጥርስ መካከል በማስገባት ምላሱን ከጉደት ማዳን ይቻላል እዚህ ላይ በእኛ ሀገር የበሽታውን ምንነት ሳናውቅ የሚያንቀጠቅጠው ሰው ስናይ እንሸሻለን፡፡ ይሔ ደግመ ኢሰባዊ ድርጊት እየፈፀምን እንደሆነ ልንረዳ ይገባል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው በሽታው ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፍና በአጉል አስተሣሠብ ተይዘው ከሆነ እርግፍ አርገው ይተውት፡፡

መ.2 ማንቀጥቀጡ አልፎ ከደረሰን

 • በዚህ ጊዜ ውስጥ በሽተኛው ራሱን ስለማያውቅና የሚንቀው ቀስ ብሎ ስለሆነ አተነፋፈሱ ትክክል መሆን አለመሆኑን አይቶ ችግር ካለው በግራ ጐኑ አስተኝቶ ማየትና ምላሱ ወደ ኋላ ወደጉሮሮው ተወትፎ ከሆነ አፉ ውስጥ ገብተን ምላሱን መጐተትና መሻሻል ካሣዬ ማህረብ አፉ ላይ አድርጐ እስጉንፋስ መስጠት፡፡
 • የልብ ምቱንም መኖር አለመኖሩን ክንዱ ላይ የደም ስሩን ምት መዳሰስ
 • በፍጥነት ህመምተኛውን ወደ ጤና ድርጅት መውሰድ እስከዚያም ከላይ የተጠቀሱትን እርዳታዎች ማድረግ

መ.3 አልፎለትና ነቅቶ ደረስን

 • ማንቀጥቀጡ ከዚህ በፊት ይኑር ወይም የመጀመሪያ ህመምተኛው ወደ ጤና ድርጅት ወስደን ማስመርመር መንሴው እንዲታወቅ መርዳት ይገባል፡፡

ሠ. ህክምና ….

 • የሚጥል በሽታ የታየበት ሰው ሁሉ ወደ ጤና ድርጅት መሄድ አለባት፡፡
 • ህክምናው እንደመንሴው ይለያያል፡፡
 • ለፌል ማንቀጥቀጥ ብዙ ጊዜ መንሴው የስርአት መዛባት …………………. ስለሆነ አንድ ጊዜ ያንቀጠቅጠው በሽተኛ ማስታገሻ ……………….. ያስፈልገዋል፡፡
 • ብዙ አይነት የማንቀጥቀጥ ማስታገሻ መዳኒቶች አሉ፡፡
 • መንሴው ታውቆ ከተመንፍ የማንቀጥቀጥ ማስተገሻ ላያስፈልገው ይችላል፡፡
 • መንሰው ካልታወቀና ካልተወገደ ግን ማስተገሻውን ከ2-5 ዓመት መውሰድ አለበት እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን ማስተገሻው ከዚህ በላይ ሊወስድ ይችላል፡፡ በዚሁ ከ2-5 ዓመት ውስጥ ማንቀጥቀጥ ካልተከሠተና EEG የሚባለው የጭንቅላት ምርመራ ውጤት ጥሩ ውጤት ካሳየ በሀኪሙና በህመምተኛው ስምምነት ቀስ እያለ በመቀነስ ሊቆም ይችላል፡፡
 • አንዳንድ ህመምተኞች መድሃኒት እየወሠድን በሽታው አልታገሠም ብለው ይቀርባሉ ይህ የሚሆንበት በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዋና ዋናዎቹም
 1. መድሃኒቱ በአግባቡ ሳይወሰድ ቢቀር ምሣሌ አንድ ጊዜ መርሣት …………… የመድሃኒቱ መጠን ከአስፈላጊው ሲያንሰ
 2. መድሃኒቱ አስፈላጊውን በሽታውን የሚከላከል መጠን ሳይደርስ ሲቀር ……
 3. ያልተወገደ መንሴ ሲኖር ወዘተ
 • የማንቀጥቀጥ ማስተገሻው ከአንድ በላይ መድሃኒት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
 • አንዳንዶቹ መድሃኒቶች የማይዘዝ ባህር ይኖራቸዋል፡፡ ይሔ የሚጠበቅ የጐን ጠንቀ (side effect) ነው
 • የማንቀጥቀጥ በሽተ አንዳንድ ጊዜ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡

I believe that a simple and unassuming manner of life is best for everyone, best both for the body and the mind.

Albert Einstein

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and typesetting industry. Lorem Ipsum has been the industry's standard dummy text ever since the 1500s, when an unknown printer took a galley of type and scrambled it to make a type specimen book. It has survived not only five centuries, but also the leap into electronic typesetting, remaining essentially unchanged. It was popularised in the 1960s with the release of Letraset sheets containing Lorem Ipsum passages, and more recently with desktop publishing software like Aldus PageMaker including versions of Lorem.

Follow Us

Subscribe Our Newsletter

Amazing Deals, Updates & Freebies In Your Inbox

MEDICAL's Poll

Which hospital is the best in 2019?
logo

Download Newskit App

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and
typesetting industry.

banner

Social & newsletter

Search