Medical

ኦቲዝም

ኦቲዝምን በአጭርና በግልፅ ቋንቋ ይህ ነው ብሎ ማስቀመጥ ይከብዳል ምክንያቱም በህመሙ የተጠቁ ሠዎች የተለያዩ ምልክቶች የሚታይባቸው ሲሆን በአንዱ ኦቲስቲክ ተጠቂ ላይ የታየው የጤና ተግር በሌላኛው ላይ ላይከሠት ይችላል፡፡ በተለምዶ በሀገራችን የአዕምሮ ህመም ተብሎ ከሚጠራው የጤና ችግር ፍፁም የተለየ ሲሆን ኦቲዝም (Autism) የአንጐልን መረጃን ወደ ውጤት የመቀየርን ሂደት የሚያዛባና የተለያዩ የNerve ህዋሣት ተቀናጅተው የሚሠሩበትን ሂደት የሚያስተጓጉል የጤና እክል ነው፡፡ በመላው ዓለም የተለያዩ ጥናቶች የተደረጉ ሲሆን አንዳቸውም ግን በእርግጠኛነት ይህ ችግር እንዴት እና በምን ምክንያት ሊከሠት እንደሚችል ተገቢ መልስ አላስገኙም፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ኦቲዝም በgene HL-መል ላይ በሚከሠት Mutation (ቅየጣ) ምክንያት ሊከሠት እንደሚችልና ይህም በመሆኑ የችግሩ ሠላባ ከሆነ ቤተሠብ የሚወለዱ ልጆች ምናልባትም ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል በበለጠ መልኩ ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃዎቹ ያሣያሉ፡፡ እነዚህ ቅየጣ የተከሠተባቸውን ዘረ-መሎችን ለይቶ ማወቅ በጣም ውስብስብና አዳጋች በመሆኑ የኦቲዝምንም ምክንያት ነጥሎ ይህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ የአሜሪካው CDC ማዕከል ሪፖርት እንደሚያሣየው በአሜሪካ ከ1000 ሺህ ሠዎች ውስጥ ዘጠኙ በኦቲዝም ሊጠቁ እንደሚችል ሲያሣይ በተቀረው ዓለም ደግመ የመከሠት ዕድሉ ከ1000 ሺህ ሠዎች ውስጥ ከ1-2 ነው፡፡

አንዳንድ በዘረ-መል ላይ ከተደረጉ ጥናቶች በተጨማሪ ለኦቲዝም መከሠት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚቀርቡ የተለያዩ መላምቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የሠውነታችን በሽታን ተከላካይ ህዋሣት የሚያመርቱት የተለያዩ ኬሚካሎች ምናልባትም አንጐላችንን ሊያጠቁትና ይህንን ችግር ሊፈጥሩ ይችላል የሚል ሲሆን ከተለመደው የአንጐል አስተዳደግ ፍጥነት በተለየ መልኩ የሚያድግ አንጐል ለችግሩ መንስኤ ይሆናል፡፡ የሚሉ አሉ በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት በፅንሡ ላይ ከፍተኛ ጉዳትን የሚያስከትሉ በተለያዩ ተዋህስያን የሚከሠቱ ኢንፌክሽኖች፣ የፀረተባይና በተለያዩ የኘላስቲክ ምርቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች፣ ከተለያዩ ፋብዘካዎችና ሞተሮች የሚወጣ ጭስ፣ አልኮዎል መጠጥ፣ ሲጋራ አደንዛዥ ዕፆች፣ የተለያዩ መድኃኒቶች የመሣሠሉት ምናልባትም የኦቲዝምን ችግር እንዲከሠትና እንደባባስ ሊያደርግ ይችላል የሚሉ መረጃዎች ቢኖርም በአንፃሩ ደግሞ ይህንን የሚቃወምና በመረጃ እነዚህ ነገሮች ለኦቲዝም መከሠት በምክንያትነት መቅረብ እንደሌለባቸው የሚከራከሩ አሉ፡፡

የኦቲዝም ምልክቶች በአንጐል ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ሥርዓቶች በአግባቡ ሣይደብሩ ሲቀሩ ሊከሠቱ እንደሚችሉ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡

ወንዶች እስከ 4 እጥፍ የሆነ ከሴቶች ጋር ሚነፃፀር በችግሩ የመጠቃት ዕድል አላቸው

 

የኦቲዝም አይነቶች

ኦቲዝም ከአምስቱ Pervesine Development Disordered (PDD) ውስጥ አንዱ ሲሆን ተጠቂዎቹን ለመከፋፈል አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም አንዳንዶቹ የህመሙ ምልክቶች በተለያዩ ደረጃ ውስጥ በሚገኙ የችግሩ ሠለባዎች ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በIQ /የአዕምሮ መመዘኛ ጥያቄ/ መሠረት የኦቲዝም ተጠቂዎችን ዝቅተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ Functioning Autism በማለት መከፋፈል ይቻላል፡፡ በተጨማሪም አንድ ኦቲስቲክ የሆነ ሠው በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ምን ያህልየሌላ ሠው እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል በሚል መመዘኛ የተለያዩ ደረጃዎችን ማውጣት ይቻላል፡፡

Savantism /ሣቫንቲዝም/ በተባለው የኦቲዝም አይነት የተጠቁ ሠዎች በሙዚቃ፣ በስነጥበብና ከቁጥር ጋር በተያያዙ ስሌቶች በጣም የተካኑ ሲሆን የሚገርመው ነገር እነዚህን ተሠጥኦዎች ያለምንም አስተማሪና ልምምድ መስራት መቻላቸው ነው፡፡

የኦቲዝም ምልክቶችና ፀባዮች

የኦቲዝም ምልክቶች በአንድ ህፃን ላይ በአብዛኛው ጊዜ ከ6 ወር ጀምሮ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መስተዋል የሚጀምሩ ሲሆን ከ2-3 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ ችግሩን መረዳት ይጀምራሉ፡፡ የዚህ ችግር ሠለባዎች የተለያዩ የመሠረታዊ ክህሎትና ጥበባቸው በአንፃሩ ከጤነኞች ጋር ሲነፃፀር በጣም የቀነሠ ሲሆን ማህበራዊ ግንኙነትን ለመፍጠር ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡

 

ማህበራዊ ዕድገት

የኦቲዝም ተጠቂዎች ራሣቸውን ከማህበረሠቡ ጋር አቀናጅቶ ለመኖር በጣም የሚከብዳቸው ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ ብቸኝነትን ይመርጣሉ፡፡ በጣም ከሚቀርቡት ሠው በስተቀር ለሌሎች ሠዎች እምብዛም ትኩረትን አይሠጡም፡፡ ይህንን ሁኔታ ቴምኘል ግራንዲን የተባለች የኦቲዝም ተጠቂ ስትገልፀው የሌሎችን ሠዎች ማህበራዊ ግንኙነትና እድገት መረዳት በጣም እንደሚያዳግታትና እራሷንም አንደ ብቻውን ማረስ በተባለችው ኘላኔት ላይ እንደተላቀቀ አንትሮፖሎጂስት ወይም ተመራማሪ እንደምታይ አስታውቃለች፡፡ እነዚህ ችግሮች በጣም በትንሽ እድሜ ላይ መታየት የሚጀምሩ ሲሆን የችግሩ ሠለባዎች

አብዛኛውን ጊዜ ሲስቁ አይስተዋልም

ሠዎችን ትኩር ብለው አያዩም /አይን ለአይን መተያየትን አይፈልጉም/

በአካባቢያቸው ለሚፈፀሙ ድርጊቶች እምብዛም ትኩረትን ላይሠጡ ይችላሉ

ስማቸው ሲጠራ እንኳን አልፎ አልፎ ካልሆነ ምላሽ አይሠጡም

በቀላሉ ነገሮችን መግለፅ ለምሣሌ ዕቃን ጠቁሞ ማሣየት የመሣሠሉትን ለማድረግ ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡

እነዚህ ህፃናት ከ3-5ኛ ዓመት ላይ ሲደርሱ ማህበረሠቡን የመረዳት ችሎታቸው በጣም አነስተኛ ቢሆንም የሌለን ሠው እንቅስቃሴና ንግግር በተወሠነ መልኩ ለመኮረጅና ለማስመሠል ይሞክራሉ ለአንዳንድ ነገሮች ምላሽ መስጠት ይጀምራሉ በተወሠነ እንቅስቃሴዎች ለመግባባት ይጥራሉ፣ ሌሎች ሠዎችን በጥቂቱ ማቅረብ የሚጀምሩ ሲሆን ነገር ግን በቅርበት ከሚንከባከባቸው ሠው ጋር የበለጠ ቁርኝነትን ይፈጥራሉ፡፡

High Functioning ኦቲዝም በተባለው ዓይነት የተጠቁት ደግመ በከፍተኛ ሁኔታ በብቸኛነት የሚጠቁ ሲሆን ጓደኛ ማፍራትና ጓደኝነትን ጠብቆ መሄድ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናቶች እንደሚያሣይት የአዕምሮ ዘገምተኛነት ያለባቸው ኦቲስቲክ ሠዎች የሀይለኛነና ፀበኛነት የመበጥበጥና ዕቃዎችን የመሠባበር ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡

 

ከሌሎች ሠዎች ጋር መግባባት

ከ1/3 እስከ ግማሽ የሚሠርሱት የችግሩ ተጠቂዎች ከሌሎች ሠዎች ጋር ለመግባባት የሚያስችላቸውን መሠረታዊ የቋንቋ ክህሎት ያላቸውም፡፡ ከመጀመሪያ ዓመታቸው ጀምሮ የተለያዩ ድምፆችን ላያሠሙ ይችላሉ፣ ያልተለመዱ ምልክቶችን ማሣየትና ያልተቀናጁና ትርጉም የማይሠጡ ቃላትን ሊያሠሙ ይችላሉ፡፡ በ2 እና 3ኛ ዓመታቸው ላይ አልፎ አልፎ የሚደጋገሙና ብዙም የማይለያዩ ድምፆችንና ቃላትን ይፈጥራሉ፡፡ ምልክቶችን ከቃላት ጋር ማጣመር በጣም ሲከብዳቸው ይስተዋላል፣ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሲጠይቁ አይስተዋልም፣ የሚያስቡትን ነገር ለሌሎች ለማካፈል አይችሉም በተደጋጋሚ ሌሎች ሰዎች የሚጠሯቸውን ቃላት በትክክል ወይም አገላብጠው ሲደጋሙ ይታያሉ፡፡

 

ተደጋጋሚ ድርጊቶች

የኦቲዝም ተጠቂዎች ተመሣሣይነት ያላቸውን ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ሲያደርጓቸው ይስተዋላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ

ተደጋጋሚ እንስቃሴዎች፡- በተደጋጋሚ ማጨብጨብ፣ ተመሣሣይ ድምፅ ማሠማት ሠውነትን ማወራጨት፣ አንገትን ማወዛወዝ የመሣሠሉት

በጨወቻዎች ተመሣሣይ ጨዋታን መምረጥ ለምሣሌ በመስመር መደርደርና ማፍረስ እንደገና መደመር

የተለያዩ የዕለት ተዕለት እንስቃሴዎችን ማመሣሠል፡፡ ለምሣሌ ተመሣሣይ ልብሶችን ለመልበስ መፈለግ፣ በየቀኑ አንድ አይነት ምግብ ለመመገብ መፈለግ

በተወሠኑ ነገሮች ላይ ማተኮር፡፡ ለምሣሌ አንድ የተወሠነ የቴሌቪዝን ጣዕቢያ ብቻ መርጦ በተደጋጋሚ ማየት በአንድ አሻንጉሊት ወይም መጫወቻ ብቻ ለመጫወት መፈለግ

አንዳንድ የኦቲዝም ተጠቂዎች በተደጋጋሚ፣ ራስን ለጉዳት የሚያጋልጡ እንደ አይናቸውን በከፍተኛ ሁኔታ መምታት፣ ቆዳን በሹል ክር መውጋት፣ እጅ መንከስ፣ ጭንቅላትን ከተለያዩ ነገሮች ጋር ማጋጨት የመሣሠሉትን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

የሌሎች ሠዎችን ሁኔታና ውስጣዊ ፍላጐት ተረድተው የራሣቸውን አስተያየት ሲሠጡ አይታይም

ለተለያዩ ማህበረሠባዊ ህጐች ተገዢ አይደለም ወይም ደንታ የላቸውም

ለሌላ ሠው ጭንቀት ወይመ ሀዘን መልስ አይሠጡም

ነገሮችን አገናዝቦ ወደፊት ምን ይከሠታል የሚለውን መገመት ይከብዳቸዋል

ለለውጥ መዘጋጀትና ስለወደፊት ማሠብ ብዙም አይስተዋልባቸውም

አብዛኛውን ጊዜ ብቸኛነትን ይመርጣሉ

በንግግር ውስጥ ተሣታፊ አይሆኑም

ከለውጥና አዲስ ሁኔታ ጋር ራስን ማስማማት አለመቻል ይታይባቸዋል

ብዙ ጊዜ ምናባዊ እይታቸው ትንሽ ነው፡፡ በአካባቢያቸው ያላውን አለም በአግባቡ ለመረዳትና ለመግባባት በጣም አዳጋች ይሆንባቸዋል

በአንዳንዶች ላይ የMood (ፀባይ) መለዋወጥ፣ የአዕምሮ ዘገምተኛነት፣ የሚጥል በሽታ፣ የእንቅልፍ መዛባት ሊከሠት ይችላል

የችግሩን ተጠቂ ለመለየት የሚረዱ ነጥቦች

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የችግሩ ሠለባ ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ወጣ ያለ ፀባይ ከ18ኛው ጀምሮ መለየት ይጀምራሉ፡፡ ከ20-25% የሚሆኑት ደግሞ ልጆቻቸው 24ኛው ወር እስኪሞላቸው ድረስ ይህንን ችግር መለየት ይችላሉ፡፡

image
image

አመልካች ሁኔታዎች

12 ወር አካባቢ የተጠጋ ዕድሜ ያለው/ት ህፃን ምንም አይነት ጤነኛ ህፃናት የሚፈጥሯቸውን የተለያዩ ድምፃች የማይፈጥሩና የሚያሠው ከሆነ፣ የተለያዩ በምልክት የሚከናወኑ ድርጊቶችን ለምሣሌ ዕቃዎችን መመጠቆምና እንዲሁም እጅን አወዛውዞ ሠላምታ መስጠት የመሣሠሉትን ማድረግ አለመቻል፡፡

በ16ኛው ወራቸው ህፃናት ምንም አይነት ቃላትን የማይናገር ከሆነና በ24ኛው ወራቸው ደግመ ሁለት ቃላትን አገጣጥመው መናገር የማይችሉ ከሆነና ማንኛውም ለቋንቋና በተለያዩ ምልክቶች የሚዳረጉ ማህበራዊ ግንኙነቶችን በማንኛውም ዕድሜ ላይ እያሉ ካጡ እነዙህ ሁኔታዎች ለችግሩ አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ችግሩን ለማረጋገጥ የሚጠቅሙ መፈተኛ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን እንደ አሜሪካና ጃፓን ያሉ ሀገራት ሁሉም ዕድሜያቸው ከ18-24 ወር ለደረሠ ህፃናት Autism (ኦቲዝም) እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ለማረጋገጥ የተለያዩ መመዘኛዎች ይሠጣቸዋል፡፡ በሀገረ እንግሊዝ ደግሞ የህፃናቱ ቤተሰቦችና ሐኪሞች ችግሩ በአንድ ህፃን ላይ ተከስቷል ብለው ከተጠራጠሩ ወደ ጤና ተቋማት በመውሰድ መመዘኛዎቹን እንዲወሰዱ ያደርጓቸዋል፡፡             

 

  ህክምና

 

ኦቲዝምና ለማከም ተብሎ የተዘጋጀ መድኃኒት የሌለ ሲሆን ዋንኛ የህክምናው አላማ የችግሩን ሠለባ በተለያዩ ማህበራዊ ክህሎቶች እንዲዳብርና የቀን ተቀን እንቅስቃሴውን ከተለያዩ ዕክሎች የፀዳ እንዲሆን በማድረግ ወደፊት ራሱን ችሎ ኑሮውን መምራት እንዲችል ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ህክምናዋንኛ ተዋንያዎቹ ቤተሰብና የልዩ ትምህርት የልዩ ትምህርት መስጫ ተቋማት ናቸው፡፡ ለኦቲዝም ተጠቂዎች የሚዘጋጁ የትምህርት ኘሮግራሞች ተልዩ መልኩ የሚቀረፁ ሲሆን ለተጠቂዎቹ ከህፃንነታቸው ጀምሮ በጥልቀትና ተያያዥነት ባለው መልኩ መስጠቱ ከፈተኛ ውጤት እንደመዘገብ አድርጓል፡፡ ህፃናቱ ጠንቃቃ እንዲሆኑና ማህበራዊ ክህሎታቸው በሠፊው እንደሞከር ከማስቻሉ በተጨማሪ የተለያዩ መሠረታዊ የስራ እውቀቶችን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል፡፡ የጤና እክሉ የሚያስከትላቸውን የተለያዩ ምልክቶች በመቀነስ አዳዲስ ፀባዮችን እንዲለምዱ እነዚህ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በአሜሪካ የተደረገ አንድ ጥናት እነዚህ ልዩ የትምህርት ኘሮግራሞችን በአግባቢ ለአንድ የኦቲዝም ተጠቂ በህይወት ዘመኑ ለመስጠት እስከ 3.77 ሚሊዮን ዶላር ሊፈጅ እንደሚችል አጣይቷል ይህም ምን ያህል የችግሩን ሠለባ ብቁ ዜጋ ለማረግ ከፍተኛ ውጤት እንደሚጠይቅ ያሣያል፡፡ ከእነዚህ የትምህርት ኘሮግራሞች በተጨማሪ ለህክምናው መድኃኒት ለማግኘት የሚዳረገው ጥረት እንደቀጠለ ሲሆን በአይጦች ላይ የተዛባን ዘረ-መል በትክክለኛ በመተካት የኦቲዝምን ህመም ምልክቶች በተወሠኑ መልኩ መቆጣጠር እንደተቻለ የሚያሣዩ መረጃዎች ወጥተዋል ይህም ውጤት ወደፊት በዘርፉ ለሚከናወኑ ጥናትና ምርምሮች አበረታችና ተስፋ ሠጪ ነገሮችን ማምጣቷ ተጠቁሟል፡፡

 

የህክምና ውጤቶች

 

ይህ ከላይ ያየነው የህክምና ኘሮግራም በችግሩ የተጠቁ ህፃናት ቀስ በቀስ ከማህበረሠቡ ጋር መቀራረብና መግባባት እንዲችሉ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች ከ3-25% የሚደርሱ የችግሩ ሠለባዎች በከፊል ከችግሩ ሊወጡ እንደሚችሉ ያሣያሉ በተለይም  በIQ /የአዕምሮ መመዘኛ ፈተና/ ከግማሽ በላይ /50%/ ውጤት ያላቸው ኦትስቲክ ሠዎች በእነዚህ ኘሮግራሞች ሲታቀፉ ወደፊት ከፍተኛ ለውጥ የማምጣት እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በእንግሊዝ /ከ1980-2004/ በ68 አዋቂ የኦቲዝም ተጠቂዎች ላይ በተደረገ ጥናት /ሁሉም የIQ ውጤታቸው ከ50 በላይ የነበረ ነው/ 12% የሚሆኑት አዋቂ ከሆኑ በኋላ ያለምንመ እርዳታ ራሣቸውን ችለው ህይወታቸውን መምራት ችለዋል፡፡ 10%የሚሆኑት ደግሞ ጥቂት ጓደኞችንን ያፈሩ ሲሆን በጥቂት እርዳታ ስራቸውን እየሠሩ ህይወታቸውን ገፍተዋል፡፡ 19% የሚሆኑት በፍፁም ነፃነት በቤት ውስጥ ከቤተሠቦቻቸው ጋር የነበሩ ሲሆን 40%የሚሆኑት በህክምና ተቋማት 12%ደግመ በከፍተኛ የተሟላ አገሉግሎት መስጫ ህክምና ተቋማት እንክብባቤ ውስጥ ነበሩ፡፡ ታድያ የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሣየው የህክምናው በተወሠነ መልኩ ውጤታማ እንደሆነና ራሣቸውን የሚችሉ የችግሩ ሠለባዎችን ማፍራት እንደሚቻል ያሣየ ነው፡፡ በአጠቃላይ ህክምናው የጤና እክሉ ያለበት ሠው ከማህበረሠቡ ወጣ ያለውን ፀባዩን በማስተካከል ተቀባየነትና መግባባት የሚያስችለውን ክህሎት እንዲለምድ በማድረግ የቋንቋ፣ የማህበራዊ አስተሣሠብ ክህሎት፣ የአካል ብቃትና የስራ ችሎታዎችን እንደያዳብር ይሆነዋል፡፡ እነዚህ ህክምናዎች ልክ ችግሩ እንደተከሠተ በጣም በህፃንነት ቢጀምሩ የሚያስገኙት ውጤት ከፍተኛ ነው፡፡

 

የተለያዩ የዘርፉ ምርምሮች

 

የትኛው ዘረ-መል ላይ የሚከሠቱ ለውጦች በኦቲዝም የመያዝ ዕድልን እንደሚፈጥሩ ለማወቅ ሠፊ ጥናቶች እየተደረጉ ሲሆን በተጨማሪም በአንጐላችን ውስጥ የሚከሠቱ ባዮሎጂካላዊ የኦቲዝምን አመላካች ንጥረ ነገሮች ለወሊድ ወቅት ለመለያየትና የትኛው ህፃናት ለችግሩ ሊጋለጥ ይችላል የሚውን ለማወቅ ጥናቶች እየተደረገ ነው በአጠቃላይ የተለያዩ የአንጐል ክፍሎች ገና ሲፈጠሩ ጀምሮ እየጐለበቱና እየዳበሩ ሲሄዱ በጋራ እርስ በእርስ ያላቸው መስተጋብር የትኛው ክፍል የትኛውን ተግባር ይቆጣጠራል የሚለውን በደንብ ለይቶ በማውጣት ለችግሩ መፍትሔ የማፈላለግ ሂደት ቀጥሏል

I believe that a simple and unassuming manner of life is best for everyone, best both for the body and the mind.

Albert Einstein

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and typesetting industry. Lorem Ipsum has been the industry's standard dummy text ever since the 1500s, when an unknown printer took a galley of type and scrambled it to make a type specimen book. It has survived not only five centuries, but also the leap into electronic typesetting, remaining essentially unchanged. It was popularised in the 1960s with the release of Letraset sheets containing Lorem Ipsum passages, and more recently with desktop publishing software like Aldus PageMaker including versions of Lorem.

Follow Us

Subscribe Our Newsletter

Amazing Deals, Updates & Freebies In Your Inbox

MEDICAL's Poll

Which hospital is the best in 2019?
logo

Download Newskit App

Lorem Ipsum is simply dummy text of the printing and
typesetting industry.

banner

Social & newsletter

Search